GERD

ማውጫ መቅድም 10 በPietro Salini GERD፣ ወደ ሀይልነት፣ ልማት እና የወደፊት ተስፋ የሚቀየር ውሀ ምዕራፍ 1 18 GERD፣ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምዕራፍ 2 34 GERD፣ ከማይቻለው በላይ ምዕራፍ 3 72 በሰዎች ትከሻ ላይ ያረፈ ምዕራፍ 4 92 በአለም ጫፍ ላይ የሚገኝ ምዕራፍ 5 112 Webuild በኢትዮጵያ፡ ለ70 ዓመታት ሀገሪቱን እያገለገለ ያለ

• ከበስተጀርባ ያለው ዋናው ግድብ ሆኖ ጥቁር አባይን ከሚሸፍኑት ከሁለቱ ድልድዮች መካከል አንደኛው

• ዋናው ግድብ እና የተከለለ የውሀ ማስወጫ/ማስተንፈሻ

• የዋናው ግድብ የውሀ ማስወጫ/ማስተንፈሻ

WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 10 መቅድም ወደ ሀይልነት፣ ልማት እና የወደፊት ተስፋ የሚቀየር ውሀ በPietro Salini፣ የWebuild CEO 11 ኃይል የሚያመርት ግድብ፣ ወደ 120 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ላላት ታላቅ ሀገር በዋጋ የማይተመን ቅርስ የሆነውን ፕሮጀክት በማስቀጠል እንዲረከብ አድርገዋል። በጣና ሀይቅ አቅራቢያ በነበርንበት በዛ ሞቃታማ ቀን ከአስር ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ኮንክሪት ያለውን ግድብ፣ ከ170 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝመውን ሰው ሰራሽ ሀይቅ እና የመላው ሀገርን የኤሌክትሪክ ሀይል በእጥፍ ለማሳደግ የሚያስችል የኃይል ማመንጫ ለማሰብ ይቅርና ለመገመት በመጀመሪያ ለምናብ ፈታኝ የነበረ ቢሆንም ከዚያ በኋላ ግን የምህንድስና ስራ ብቻ ነበር። ነገር ግን ምናብ በራሱ በራዕይ ለሚኖሩ እና ከአሁን በፊትም ቢሆን ወደፊትን ለመኖር ለሚጠቀሙበት ሰዎች አስፈላጊው አመለካከት ነው። GERD፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተወለደው ከራዕይ ነው፡ ከአፍሪካ እጅግ ብዙ ህዝብ ካላቸው ሀገራት ከአንዷ ፣ ሀይል ለማመንጨት እና ልማት ለማምጣት የተፈጥሮ ሀብቶቿን በአግባቡ መጠቀምን ከመረጠ መንግስት የተወለደ ራዕይ። በእርግጥም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአፍሪካ ግዙፉ የውሃ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን ብልህነት፣ ድፍረት እና ራዕይ የሀገርን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚቀይር የሚያሳይ ተጨባጭ ምልክት ነው። GERD የሚፈስ ሃይል ነው፣ ቤቶችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና ፋብሪካዎችን የሚያበራ ብርሃን ነው፣ ለኢትዮጵያ ብሎም ለመላው የምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት አንቀሳቃሽ ነው። ያ ምሽት አሁንም በአእምሮዬ/ ትውስታዬ ውስጥ ተቀርጿል። ለኢትዮጵያ ልክ እንደ ብዙ ሌሎች ከዓመታት በፊት እንደተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ሁሉ አስፈላጊ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ የሆነውን የበለስ ባለ ብዙ ዘርፍ ፕሮጀክት በገነባንበት ቦታ በጣና ሀይቅ አቅራቢያ ላይ ነበርኩ። ከጎኔ የወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የነበሩ ሲሆን ቀደም ሲል ያሰብናቸውን፣ የነደፍናቸውን እና የገነባናቸውን ብዙዎቹን የአገሪቱን እጅግ አንገብጋቢ ስራዎች እውን እንድናደርግ ያስቻሉ ታላቅ ራዕይ ያላቸው የሀገር መሪ ነበሩ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በድንገት ቆሙ እና እንዲህ ብለው ነገሩኝ፡ “ለዚህች ሀገር ሕልም አለኝ፡ የሁሉንም ወንዞቿን ውሀ ወደ ነዳጅነት መቀየር- የማያልቅ የሀይል ምንጭ እንዲሰጡ፣ ለኢንዱስትሪዎች ፍጆታ በቂ ሀይል እንዲሰጡ፣ ለእያንዳንዱ ቤት ብርሀን እንዲሰጡ እና ለእያንዳንዱ ወጣት ትውልድ ተስፋ እንዲሆኑ የማድረግ ህልም። በዚህም ምክንያት በአባይ ወንዝ ላይ የሆነ አስደናቂ፣ ልዩ፣ እጅግ በጣም ልዩ ሆነ ነገር ለመገንባት ፈለግኩ። ይህን ንድፍ ለማዘጋጀት ምን ያህል ጊዜ ይወስድብዎታል?”” ወቅቱ ሞቅ ያለ፣ ብሩህ ምሽት ነበር፣ እናም በዚያ ቅጽበት የመላው ሕዝብ ሕልም የሆነው GERD ተወለደ። አንድ አመት ሳይሞላው መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፤ ግን ሌላኛው ታላቅ ሰው፣ ሌላኛው ታማኝ ወዳጅ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሊ ያንን ራዕይ ተቀብለው አስቀጥለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግዙፍ ተግዳሮቶችን በማለፍ ዛሬ ወደ ታሪክ የሚገባውን ፕሮጀክት፣ ከሦስት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች የሚበልጥ መቅድም |

መቅድም | 13 WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 12 የውሃ ኃይል ማመንጫ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን መሪ የታዳሽ ኃይል ምንጭ ሲሆን የካርቦን ልቀትን በመቀነስ ውስጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ላሉት የውሃ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ምስጋና ይግባቸውና Webuild 14,000 ሜጋ ዋት የተገጠመ አቅም በማመንጨት ከ23 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ንፁህ እና ተደራሽ ሃይል በማቅረብ እና የCO2 ልቀት መጠንን በዓመት 13 ሚሊዮን ቶን ለመቀነስ እገዛ ያደርጋል። ልክ እንደ ሌሎች ቦታዎች ሁሉ በአፍሪካ ለሀይል/ ኢነርጂ ተደራሽ መሆን የቴክኖሎጂ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለትምህርት፣ ለጤና እና ለሰው ልጅ ክብር አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው። ከጥቁር አባይ የሚፈሰውን ውሃ ወደ ኤሌትሪክነት መቀየር ህዝቦችን አንድ ለማድረግ እና አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር የሚያስችል የወደፊት ድልድይ ይሆናል። GERD በምህንድስና ታሪክ ውስጥ ሁልጊዜም የሚነገር ታሪክ ብቻም ሳይሆን ከምንም በላይ ስራው እውን ሲሆን ለሚያዩና ለሚያመሰግኑ ሰዎች በትውስታቸው ውስጥ የተለየ ነገን ማሰብ ይችላሉ። ለእኛ በWebuild ውስጥ ላለን ሰዎች ዘላቂ መሠረተ ልማት መገንባት ማለት የወደፊቱን መገንባት እንደሆነ ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው። ለእኛ Webuild የዚህን ፕሮጀክት ግንባታ መምራት ልዩ እድል እና ኃላፊነት ነበር። ስራውን የሰራነው ውስብስብ በሆነ አውድ ውስጥ፣ በአህጉሪቱ ውስጥ ካሉ እጅግ በርቀት ከሚገኙ ቦታዎች ውስጥ አንዱ በሆነው ቀደም ሲል የጠጠር መንገዶችና ተራርቀው የሚገኙ መንደሮች በነበሩበት ቦታ ውስጥ መሰረተ ልማት በመስራት፣ ቴክኖሎጂዎችና ሙያዊ ልምድ ይዘን በመምጣት ነው። የገነባነው ግድቦችን እና የኃይል ማመንጫዎችን ብቻ ሳይሆን ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታሎችን፣ መንገዶችን እና የመገናኛ ዘዴዎችንም ጭምር ሲሆን ይህም ልማትን የሚደግፍ አጠቃላይ ሥነ ምህዳር ነው። GERD እንዴት በተሻለ ሁኔታ መስራት እንዳለብን የምናውቀውን ነገር የሚወክለው ለዚህ ነው። ይህን ማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የምህንድስና ተግዳሮቶችን መፍታትን፣ የቴክኒክ ልህቀትን ከድርጅታዊ አቅም ጋር ማጣመርን ይፈልጋል። የኢትዮጵያን ግድብ በተመለከተ ይህ ማለት የጥቁር አባይን አቅጣጫ ማስቀየር፣ በሚሊዮኖች ሜትር ኩብ ውሀ የሚይዝ አርማታ መትከል፣ ከ5,000 ሜጋ ዋት በላይ ንጹህ ሀይል ማመንጨት የሚችሉ ተርባይኖችን መትከል ማለት ነው። በርግጥ GERD ለኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን ለመላው የአህጉሪቱ የኃይል ሽግግር ጠቃሚ መሳሪያ ነው።

WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 14 • የጥቁር አባይ አቅጣጫ በሚቀየርበት ወቅት የዋናው ግድብ የላይኛው እይታ

WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • ዋናው ግድብ ከኃይል ማመንጫዎች እይታ ጋር

18 ምዕራፍ 1 WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም

ምዕራፍ 1 | GERD፣ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 20 CAP 2 | 21 • አዲስ አበባ አንዴ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ከገባ በኋላ ከGERD የሚመነጨው ሃይል ኢትዮጵያን ሀገራዊ ምርቷን በእጥፍ እንድታሳድግ እና እንደ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛኒያ ላሉ ጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ሃይል እንድትልክ ያስችላታል። ኢትዮጵያ በውሃ እና በንፁህ ኢነርጂ ምርት ላይ ትኩረት በማድረግ የወደፊት እድሏን እንደገና እየቀረፀች ነው። አስደናቂ የወንዞች ትስስር እና ከ45,000 ሜጋ ዋት በላይ የሚገመት የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ያላት ሀገሪቱ ባለፉት አስርት አመታት ውስጥ የተፈጥሮ ሀብቶቿን ወደ ንፁህ፣ ተደራሽ እና ወደ ውጭ መላክ የሚችል ኢነርጂ ለማሸጋገር ያላትን ታላቅ ስትራቴጂያዊ ህልም እያሳካች ነው። ይህ በምህንድስና፣ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲ አማካኝነት የሚካሄድ የቁማር ጨዋታ አይነት ሲሆን ይህም ቀደም ብሎም ተጨባጭ ውጤቶችን ከማምጣቱም በተጨማሪ ቀደም ሲል በታሪክ ውስጥ በሀይል ድህነት የምትታወቀውን የሀገሪቱን ገጽታ በመቀየር ላይ ነው። የዚህ ሽግግር ዋና ዋና ገፀ ባህሪያቱ ትላልቅ ግድቦቹ እና ከእነዚህ ጋር የተገናኙት የውሀ ኃይል ማመንጫዎች ናቸው። እነዚህ ከፍተኛ ህልም ያዘሉ፣ በቴክኖሎጂ የላቁ ፕሮጀክቶች ሁለት ፍላጎቶችን የሚያሟሉ ናቸው፡ በአንድ በኩል ወደ 130 ሚሊዮን ለሚጠጉ ህዝቦች የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ማረጋገጥ እና በሌላ በኩል ኢትዮጵያን የመላው የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የኃይል ምንጭ ማድረግ። ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በ2024 ሀገሪቱ 5,300 ሜጋ ዋት የተተከለ አቅሟን

ምዕራፍ 1 | GERD፣ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም | GERD. THE DAM OF RECORDS 22 23 • የታችኛው ተፋሰስ እይታ የቀኝ ዳርቻ የሀይል ማመንጫ፣ ማእከላዊ የውሀ ማስወጫ/ማስተንፈሻ እና የግድቡ የላይኛው አካል/ክረስት ድልድይ በ2024 ኢትዮጵያ 5,300 ሜጋ ዋት የተተከለ አቅሟን ያለፈችና ይህም ከአስር አመታት በፊት ከነበረው በእጥፍ ብልጫ ያለው ሲሆን ያም ሆኖ ግቡ በ2037 ዓ.ም 17,000 ሜጋ ዋት አቅም ላይ መድረስ ነው። ያለፈች ሲሆን ይህም ከአስር አመታት በፊት ከነበረው በእጥፍ ይበልጣል። ነገር ግን ግቡ ከዚህ የላቀ ህልም ያዘለ ነው፥ ይህም በ2037 ዓ.ም 17,000 ሜጋ ዋት አቅም ላይ መድረስ ነው። በመሆኑም የኢነርጂ ልማት ለኢንዱስትሪ ለውጥ፣ ለድህነት ቅነሳ እና ለሥራ ዕድገት የጀርባ አጥንት ይሆናል። ምክንያቱም ሀብቶቿን መቆጣጠር የቻለች ሀገር ለወደፊት የዕድገቷን ጎዳና በተሻለ መንገድ መምረጥ የምትችል ሀገር ስለምትሆን ነው። GERD፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዚህ የልማት እቅድ የማዕዘን ድንጋይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD)፣ ግድቡን የሚያጠቃልለው የሜጋ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ሲሆን ስሙ እንደሚያሳየው የአገሪቱን ራዕይ የያዘ ሆኖ ይህም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ጉዞን ያቀፈ እና የኢነርጂ ነፃነትን የማሳደግና በአፍሪካ ቀዳሚ የዘላቂ ኢነርጂ አምራች የመሆን ፍላጎትን የሚያሳይ ነው። በ74 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የውሃ ማጠራቀሚያ አቅም እና በ5,150 ሜጋ ዋት (ከሶስት መካከለኛ መጠን ያላቸው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ጋር እኩል የሆነ) የተተከለ ሃይል የማመንጨት አቅም GERD በአፍሪካ ትልቁ እና በዓለም ላይ ካሉት ሃያ ግዙፍ የውሃ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው። የግድቡ

24 25 ምዕራፍ 1 | GERD፣ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም

ምዕራፍ 1 | GERD፣ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም | GERD. THE DAM OF RECORDS 26 27 • የባምዛ መንደር የፕሮጀክቱ ግንባታ የተደረገለት የገንዘብ ድጋፍ፥ በመንግስትና በኢትዮጵያ ህዝብ በቦንድ ሽያጭ እና ግዥ ሲሆን፣ ምንም አይነት የባለብዙ ወገን አለም አቀፍ ባንኮች ድጋፍ አላስፈለገውም። ሀይል የማመንጨት አቅም በግድቡ መሰረት ላይ በሚገኙት ሁለቱ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫዎች ላይ የተመሰረተ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ የሚመረተው ሃይል ኢትዮጵያን አገራዊ ምርቷን በእጥፍ እንድታሳድግ እና እንደ ሱዳን፣ኬንያ፣ጅቡቲ እና ታንዛኒያ ላሉ የጎረቤት አገራት የኤሌክትሪክ ሃይል እንድትልክ ያስችላል። GERD ከግዙፉ የኢነርጂ አቅም ባሻገር የፖለቲካ እና የባህል ምልክት ነው። ግንባታውም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ቦንድ በማውጣትና በመግዛት የተሸፈነ ሲሆን፣ ከማንኛውም የባለብዙ ወገን አለም አቀፍ ባንኮች ድጋፍ አላገኘም። ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያ እጣ ፈንታዋን በራሷ የመወሰን እና ወደ ልማት የወደፊት መንገድ የመመልከት ቁርጠኝነትን ያንጸባርቃል።

ምዕራፍ 1 | GERD፣ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም | GERD. THE DAM OF RECORDS CAP 2 | 28 29 • አዲስ አበባ

ምዕራፍ 1 | GERD፣ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም | GERD. THE DAM OF RECORDS CAP 2 | 30 31 • በግድቡ እና በጥቁር አባይ የዋናው ግድብ የታችኛው ተፋሰስ ምክንያት የተፈጠረው የውሀ ማጠራቀሚያ እና እይታ

ምዕራፍ 1 | GERD፣ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም | GERD. THE DAM OF RECORDS CAP 2 | 32 33 • የባምዛ መንደር

34 ምዕራፍ 2 WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም

ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 36 37 የአስራ አራት ዓመቱ ጉዞ ሲያበቃ GERD የዛውን ኃያል እና የተሟላ ግድብ ይወክላል። ሪከርድ የሰበረው ግንብ የጥቁር አባይን ጉዞ ከመግራት ባለፈ የመላ አገሪቱን ኢኮኖሚና የወደፊት ተስፋ ቀይሮታል። ኢትዮጵያ በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር ብቻም ሳትሆን ከደሀ ሀገራት ተርታ የምትሰለፍ ከጎርፍ እስከ ተደጋጋሚ ድርቅ ያሉ ጉልህ ተግዳሮቶች የሚያጋጥሟት ሀገር ነች። ያም ሆኖ ሀገሪቱ ለመልክአ ምድሯ እና በውስጧ ለሚያልፉት ታላላቅ ወንዞቿ ምስጋና ይግባውቸና ከፍተኛ የውሃ አቅም አላት። ከእነዚህም ውስጥ ጥቁር አባይ አንዱ እና በትክክል GERD የተገነባበት ወንዝ ሲሆን ግድቡ በቀላሉ ግድብ ብቻ ሳይሆን የስራዎች የተቀናጀ ስርዓት/ሲስተም ነው። ፕሮጀክቱ የሁለት ግድቦች ግንባታን ያካተተ ነው፡ ዋናው ግድብ 170 ሜትር ቁመት እና 1,800 ሜትር ርዝመት ያለው ከሮለር-ኮምፓክትድ ኮንክሪት (RCC) የተሰራ የስበት ኃይል ሲሆን ሁለተኛው ተቀጽላ/ሳድል ግድብ ደግሞ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 50 ሜትር ቁመት ያለው በድንጋይ ሙሌት ላይ አርማታ በማንጠፍ የተገነባ ግድብ ነው። ተቀጽላ/ የሳድል ግድቡ በኢትዮጵያ ኮረብታዎች ላይ የተተከለ ግማሽ ጨረቃ የሚመስል ቀስት ቅርጽ ያለው ሲሆን በግራ ጎኑ የሚገኘው ከውኃ ማጠራቀሚያ የውሀ መበታተንን የመቀነስ ተግባር ያለው ሆኖ ወደ ሱዳን የሚፈስ ጎርፍ እንዳይፈጠር ይከላከላል። አሀዞቹ ብቻቸውን የሁለቱን ግድቦች ልኬት ይይዛሉ፡ ለዋናው ግድብ 10.7 ሚሊዮን ሜትር ኩብ RCC – በሮለር የተጠቀጠቀ ኮንክሪት የተተከለ ሲሆን ለተቀጽላ/ ሳድል ግድቡ ደግሞ 15.3 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የድንጋይ ሙሌት ጥቅም ላይ ውሏል። የGERD ግንባታን በተመለከተ የWebuild የኦፕሬሽኖች ከፍተኛ ስራ አስፈጻሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ከሰሀራ በታች አፍሪካ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር የሆኑት ኢንጂነር Christian Fabio Capitanio “ግንባታው ልዩ ጥረት የሚጠይቅ ነበር” ብለዋል። “የአባይን መንገድ አቅጣጫ ቀይረናል፣ ሁለት ግድቦችን ገንብተናል፣ ትልቅ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ፈጥረናል እንዲሁም ለኢትዮጵያ አዲስ መፃኢ ዕድል ፈንጥቀናል።” ሲሉ አክለዋል። በሁለቱ ግድቦች ግንባታ ምክንያት የተፈጠረው እና አሁን የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችን የሚያንቀሳቅሰው የውሃ ማጠራቀሚያ 172 ኪሎ ሜትር የጎን ርዝመት ያለው ሲሆን 1,875 ካሬ ኪሎ ሜትር ቦታ የሚሸፍን ሆኖ 74 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም አለው። ከግድቡ በታች ያለው አማካይ ዓመታዊ የውሃ ፍሰት 50 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ይሆናል ተብሎ ይገመታል። GERD ግድብ ብቻ ሳይሆን የስራዎች የተቀናጀ የአሰራር ስርዓት ነው። የQR ኮድ ስካን GERD፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም ዙሪያ ከተገነቡት የመሠረተ ልማት ሥራዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው። የፕሮጀክቱን የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ሀይል የማመንጨት አቅም በዕጥፍ የማሳደግ አቅም ያለው የሀይል ማመንጫ የመገንባት ግብ ለማሳካት የአጠቃላይ መዋቅሩ መጠነ ዙሪያዎች ወሳኙ ሁኔታ ነበር። እነዚህ መጠነ ዙሪያዎች GERDን የዓለም ሪከርዶችን እንዲሰብር እና በአፍሪካ አህጉር ታይቶ የማይታወቅ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አስችሎታል። የመጀመሪያው ሪከርድ ከዋናው ግድብ ከራሱ መጠነ ዙሪያዎች ጋር የተሳሰረ ነው። ከላይኛው የመሬት ክፍል አንስቶ 170 ሜትር ቁመት እና 1,800 ሜትር ርዝመት ያለው ዋናው ግድብ በአፍሪካ እስካሁን ከተሰሩት ሁሉ ትልቁ ግድብ ነው። በአህጉሪቱ ውስጥ Webuild Group በኦሞ ወንዝ ላይ እንደተገነባው 250 ሜትር ቁመት ያለውና በተመረቀበት ወቅት በዓለም ረጅሙ ግድብ የነበረው ጊቤ III ያሉ ሌሎች በቁመታቸው ከGERD የሚበልጡ ግድቦችን የገነባ ቢሆንም ነገር ግን የGERD ቁመት ከላይኛው የመሬት ወለል በላይ ካለው ርዝመት ጋር ተደምሮ ፍጹም ሪከርድ አስገኝቶለታል። ሁለተኛው ምዕራፍ የተሳካው በታህሳስ 28, 2014 በዋናው ግድብ ላይ የሚሰሩት ቡድኖች በ24 ሰአት ውስጥ 23,000 ሜትር ኩብ የሚደርስ ከፍተኛ መጠን ያለው RCC በመትከል የዓለምን ሪከርድ ባስመዘገቡበት ወቅት ነበር። ይህ ከመጠነ ሰፊ ዝግጅት በኋላ የተገኘው ስኬት ታታሪነትን ብቻ ሳይሆን የግንባታ ሳይቱን የምህንድስና እና ድርጅታዊ ክህሎቶች ይመሰክራል። ሪከርድ #1 ከመሬት የላይኛው ወለል አንስቶ 170 ሜትር ቁመት እና 1,800 ሜትር ርዝመት ያለው ዋናው ግድብ በመጠኑ በአፍሪካ በይዘቱ ትልቁ በRCC የተሰራ በስበት ሀይል የሚሰራ ግድብ ነው። ሪከርድ #2 የዋናው ግድብ የግንባታ ሳይት በ24 ሰአታት ውስጥ 23,000 ሜትር ኩብ ጋር እኩል የሆነ RCC የተተከለበት በመሆን የዓለምን ትልቁን ሪከርድ ይይዛል። ማመንጫ ፕሮጀክት

38 39 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • ዋና ግድብ RCC (በሮለር የሚጠቀጠቅ አርማታ) ዝቅተኛ የሲሚንቶ እና የውሀ ይዘት ያለው፣ እጅግ ደረቅ ልዩ የአርማታ ድብልቅ ነው። ከተለመደው አርማታ በተለየ ይህኛው አርማታ አይጨመርም፣ ከዚህ ይልቅ ለመንገድ ጠርዞችና አስፋልት እንደሚደረገው በተመሳሳይና በተከታታይ ንብብሮች ይነጠፍ እና በሜካኒካል ዘዴ ይጠቀጠቃል። አጠቃቀሙ የመዋቅሩን መረጋጋትና ዘላቂነት በማረጋገጥ የግንባታ ስራውን ለማፋጠን ስለሚያስችል በግድቡ ግንባታ ላይ በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል።

ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • በ ግድቡ እና በጥቁር አባይ የዋናው ግድብ የታችኛው ተፋሰስ ምክንያት የተፈጠረው የውሀ ማጠራቀሚያ እና እይታ

ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • የግድቡ ግንባታ የመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች እና የጥቁር አባይን አቅጣጫ ማስቀየር

44 45 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • ሁለተኛው የድንጋይ ሙሌት ግድብ በኮንክሪት ገጽ

ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ 46 WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም ለኢትዮጵያ ብርሀን የሚሰጡ የውሀ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች የGERD ሥራ የጥቁር አባይን ውሀ በመገደብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ነው። ከዋናው ግድብ በታች ሁለት የኃይል ማመንጫዎች የተገነቡ ሲሆን እነዚህም አንደኛው በወንዙ የቀኝ ዳርቻ እና ሌላኛው በግራ ዳርቻ የተገነቡ ናቸው። ሁለቱ የኃይል ማመንጫዎች በጠቅላላው 5,150 ሜጋ ዋት የተተከለ አቅም እና በዓመት 15,700 ጊጋ ዋት የሚጠበቅ የማምረት አቅም የሚይዙ 13 የፍራንሲስ ተርባይኖች የያዙ ናቸው። የኃይል ማመንጨቱ የውሀ ማጠራቀሚያ ቋቱ ሙሉ በሙሉ ሳይሞላ በ2022 ተጀምሯል። ፕሮጀክቱ የተነደፈው ከ13ቱ ተርባይኖች ሁለቱ ከመጨረሻው ባነሰ የውሀ መጠን እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ የውሀ ማጠራቀሚያ ቋቱ ውሀ መያዙን እየቀጠለ እያለ የኃይል ማመንጫው ኃይል በማመንጨት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ ማስገኘት እንዲጀምር ታስቦ ነው። የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየር፣ ሀይቅ እንዲፈጠር ማድረግ የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየር እጅግ ፈታኝ ከሆኑ ስራዎች መካከል አንዱ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ግዙፍ የውሀ መጠን ለመያዝ የሚያስችል የውሀ ማጠራቀሚያ ለመፍጠር የስራ ሂደቱ በተከታታይ ዙሮች ተከናውኗል። በየወቅቱ ቁጥጥር የሚደረግበት ከ10 እስከ 15 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የውሀ የማጠራቀም መጠንን በመከተል የውሀ ማጠራቀሚያውን መሙላት አመታትን ወስዷል። ይህ ውስብስብ ስራ በተለይም የወንዙ ፍሰት ይቀንሳል ብለው የሰጉትን የታችኛው የተፋሰሱን ሀገራት በተለይም የሱዳን እና ግብፅን ስጋቶች ለመቅረፍ በየጊዜው ክትትል ይደረግበት ነበር። “ውሀው ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ አያውቅም” ሲሉ ኢንጂነር Christian Fabio Capitanio ገልጸዋል። “ተርባይኖቹ ኃይል ማመንጨት ከጀመሩ በኋላ ተርባይኑን መትቶ የሚወጣው ውሀ ወደ ታች ይለቀቅ እና የወንዙን ፍሰት መመገቡን ይቀጥላል።” የጎን አሞሌ WEBUILD: በንጹህ ኢነርጂ መሪ ተቋምY ከግድቦች እስከ ሀይል ማመንጫዎች አጠቃላይ ውስብስብ የስራዎች ስርዓትን የሚይዘው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተገነባው በውስብስብ መሰረተ ልማት ግንባታ መሪ በሆነው እና ወደ 120 ለሚጠጉ ዓመታት በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃ`ይል ማመንጫና ግድቦች ዲዛይንና ግንባታ ላይ በተሰማራው Webuild Group ነው። እስካሁን ድረስ ቡድኑ በሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ላይ ትኩረት በማድረግ በጠቅላላው 53,659 ሜጋ ዋት የተተከለ ሀይል የማመንጨት አቅም ያላቸው 318 የሀይል ማመንጫዎችን የገነባ ሲሆን ይህም የዓለማችን መሪ የታዳሽ ሀይል ምንጭ ያደርገዋል። ባለፈው እና በወደፊቱ መካከል እንደ በአርጀንቲና የሚገኘው የYacyretà ግድብ፣ Rogun ግድብ (በአሁኑ ወቅት በታጃኪስታን ውስጥ በግንባታ ላይ የሚገኝ) እና የኮይሻ ግድብ (በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በመገንባት ሂደት ላይ ያለ) የመሳሰሉ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች አሉት። በአሁኑ ወቅት በቡድኑ በመገንባት ላይ ያሉት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች የ14,000 ሜጋ ዋት ተከላ እንዲካሄድ ከማስቻላቸውም በተጨማሪ በመላው ዓለም ከ23 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ንጹህ፣ አነስተኛ ወጪ የሚያስወጣ ኃይል ለማቅረብ ያስችላሉ። በተለይም Webuild በአፍሪካ ቀንድ፣ በማዕከላዊ እሲያ እና በአውስትራሊያ ውስጥ ዓመታዊ የCO2 ልቀቶችን በ13 ሚሊዮን ቶኖች የመቀነስ አቅም ያላቸው የሀይድሮ ኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ላይ ነው። 47 ዋናው ግድብ 170 ሜትር ከፍታ እና 1800 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ተቀጽላ/ የሳድል ግድቡ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 50 ሜትር ከፍታ አለው። በአሁኑ ወቅት በWebuild Group በመገንባት ላይ ያሉት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች 14,000 ሜጋ ዋት ሀይል ከማመንጨት በተጨማሪ በመላው ዓለም ከ23 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ንጹህ፣ አነስተኛ ወጪ የሚያስወጣ ኃይል ያቀርባሉ። • የሮገን ግድብ

48 49 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • የዋናው ግድብ እና በስተ ቀኝ ዳርቻ የሚገኘው የኀይል ማሰራጫ የታችኛው ተፋሰስ እይታ

50 WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 51 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ ስለሆነም የፕሮጀክቱ የመጀመሪያው ተግዳሮት ጥቁር አባይ በዝናብ ወቅት ፍሰቱ በሰከንድ 8,000 ሜትር ኩብ መካከለኛ የፍሰት መጠን ላይ ሊደርስ የሚችል በመሆኑ ምክንያት ወንዙን በራሱ መቆጣጠር ነበር። ስለዚህም የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየር የብልሃት እና የድፍረት ውጤት ነበር። “የወንዙን የፍሰት አቅጣጫ እንደ አስፈላጊነቱ ከአንድ ዳርቻ ወደ ሌላ ዳርቻ ማስቀየርን የሚይዝ ተንቀሳቃሽ አቅጣጫ ማስቀየሪያ ስርዓት ነድፈናል።” ሲሉ አክለዋል። “ከዚያም ቁፋሮ በማካሄድና መሰረቶችን በማጠናከር የመሰረተ ልማት ግንባታውን ደረጃ በደረጃ አካሂደናል።” የግድቡ የቴክኖሎጂ ሚስጥሮች ግዙፎች እንኳን የራሳቸው ሚስጥሮች አሏቸው። የGERD ሚስጥሮች ለግንባታው ጥቅም ላይ በሚውሉ ዕቃዎች ላይ ወጥ ጥናት ከማካሄድ አንስቶ የኃይል ማመንጫውን ሁኔታ መከታተልን፣ የውሀ ግፊቱን እና ደረጃውን፣ የአርማታዎች ጥምረትን፣ የተርባይኖች በአግባቡ መስራትን እና የመሰረተ ልማቱን እያንዳንዱን ጉዳዮች ቅጽበት በቅጽበት መከታተልን እስከሚይዙት ውስብስብ የክትትል ስርዓቶች ድረስ ለፕሮጀክቱ ስራ ጥቅም ላይ የዋሉትን የቴክኒክና የምህንድስና ልህቀቶች ያሳያሉ። የስራው ልዩ ክፍል በሮለር የሚጠቀጠቅ የአርማታ ውድ መጠቀም ነው፡ በውህዶቹ ላይ ዓለም ዓቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ኤክስፐርቶችን ያካተተ ጥናት የተካሄደ ሲሆን ይህም አርማታው የሚተከልበትን በእጅጉ ያራዘመ ቢሆንም ከምርትና የዕቃዎች ጥራት ከፍተኛ ጥቅሞችን አስገኝቷል። በልዩ ባለሙያዎች የተቀናጁ የውስጥ ላቦራቶሪዎች ረዘም ያለ የተከላ ጊዜዎችና የተሻለ የሜካኒካል አፈጻጸም ቀመሮችን አዘጋጅተዋል። ጥቅም ላይ የዋሉ እቃዎች የላቀ መሆን እና የረጅም ጊዜ አገልግሎት ከሚሊዮን ቶኖች RCC ስር በሚያልፉት የዋሻ ውስጥ ኔትወርክ በተዘረጉት እጅግ ዘአመናዊ የመቆጣጠሪያ ሲስተሞች አማካኝነት የተካሄዱት ሙከራዎች ውጤት ናቸው። በዋናው ግድብ የስዕል ማዕከሎች ውስጥ የሚያልፍ ሰው እያንዳንዱን የመዋቅሩን እንቅስቃሴ የሚተነትኑ እና የውሀ ግፊቱ እንዴት እንደሚመልስ በትክክል የሚያረጋግጡ ተከታታይ መሳሪያዎችን ያገኛል። እነዚህ መሳሪያዎች ለምሳሌ በተለያዩ የኮንክሪት ብሎኮች መካከል ያሉትን መገጣጠሚያዎች ትክክለኛነት ይመረምራሉ እንዲሁም በግድቡ መዋቅር ውስጥ ያሉትን የሚሊሜትር ለውጦች ይመዘግባሉ። • የዋናው ግድብ ክረስት እና ከታች/በመሰረቱ ላይ ያሉት ሁለቱ የሀይል ማሰራጫዎች በግድቦቹ ግንባታ ምክንያት የተፈጠረው የውሃ ማጠራቀሚያ 172 ኪሎ ሜትር የጎን ርዝመት እና 74 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም አለው።

ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 53 | GERD. LA DIGA DEI RECORD • THE DAM OF RECORDS 52 • የRCC ቴስት ሲሊንደሮች Antonio Passarani የግንባታ ሥራ አስኪያጅ GERD የQR ኮድ ስካን የጎን አሞሌ የዓለም ሪከርድ መነሻ “በፕሮጀክቱ መጀመሪያ ላይ ያጋጠመን ተግዳሮትት” ሲሉ በማስታወስ “የጥቁር አባይ ወንዝን የፍሰት አቅጣጫ በማስቀየር 10.7 ሚሊዮን ሜትር ኩብ RCC ማምረት እና ይህን በቦታው ላይ መትከል ነበር።” በእንደዚህ አይነቱ ፕሮጀክት ውስጥ ፍጥነትና አደረጃጀት የሁሉም ነገር ቁልፍ ነው። እነዚህ ችሎታዎች በ2014፣ ከአዲስ ዓመት በፊት ከፍተኛው የመገለጫ ደረጃቸው ጫፍ ላይ ደርሰው ነበር። “አንዴ በ2013 ማምረት ከተጀመረ በኋላ” ሲሉ ይቀጥላሉ Passarani “የRCC ማምረቱን የተለያዩ ደረጃዎች ሚሊዮን በሚሊዮን እየተከታተልን በቢሮ ውስጥ ባለው ኋይት ቦርድ ላይ መመዝገብ/ ምልክት ማድረግ ጀመርን። ከዚያ በኋላም ውጤቶቹን በጥቁርና ነጭ መጻፍ የተሻለ ስራ ለመስራት ማነቃቂያ ሆነ።” በርግጥም ደረጃ በደረጃ የግንባታ ሳይቱ አሁን እስከደረሰበት ከፍተኛ ደረጃ ድረስ ድርጅታዊ ሞዴሉን ማጥራት እና አፈጻጸሙን ማሻሻል ችሏል። “የአሰራር ስርዓቱ በአግባቡ ከጠራ በኋላ” ሲሉ የኮንስትራክሽን ሥራ አስኪያጁ በማስታወስ “የጠረጴዛ ሰዓቱን ዜሮ ላይ ሞልተን ውጤቱን ለማየት 24 ሰዓቶች ስንጠባበቅ ቆይተናል። በታሕሳስ 28, 2014 ንጋት ላይ ከሙሉ ቀን ያልተቋረጠ ስራ በኋላ ለግድቡ RCC በመትከል የዓለማችንን ሪከርድ አሳክተናል።” ታህሳስ 28፣ 2014. የWebuild Group የGERD የኮንስትራክሽን ሥራ አስኪያጅ የሆኑት Antonio Passarani ይህን ልክ ዛሬ ላይ እንዳለ ሁሉ ያስታውሱታል።

54 55 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • የቀኝ ዳርቻ ሀይድሮሊክ የኃይል ማመንጫ

57 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 56 ከግድቡ ጫፍ አንስቶ እስከ ግድቡ መሠረት ድረስ የተዘረጉት እጅግ ዘመናዊ ፔንዱለሞች ድረስ የፕሮጀክቱ መሳሪያዎች እያንዳንዱን ትናንሽ እንቅስቃሴዎች ይመዘግባሉ። ሁሉም እንቅስቃሴዎች እና ጫናዎች መመዝገብ ብቻ ሳይሆን በመቆጣጠሪያ ማዕከሉ ውስጥ ወደሚገኘው የመረጃ ቋት ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ይህም በስተቀኝ ዳርቻ በግድቡ የታችኛው ክፍል በሚገኘ የምህንድስና ግንባታ ቢሮ ውስጥ ያለ የአሰራርና የቴክኖሎጂ ዋና ማዕከሎች ዝግጅት ነው። እዚህ የመዋቅሩን ሁኔታ በሪል ታይም ለማረጋገጥ ዳታ ይሰበሰባል፣ ይመዘገባል እንዲሁም ይተነተናል። • የታችኛው ማስወጫ በስራ ላይ እያለ፣ የግራ ዳርቻ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ በመዋቅሩ ውስጥ የተተከሉት የተራቀቁ የመቆጣጠሪያ ሲስተሞች የአገልግሎት መስጫውን እውነተኛ ገጽታ በጨረፍታ ያሳያሉ።

59 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • የዋናው ግድብ የሥረኛው ክፍል ግንባታ Franco Cetrangolo የግድቡ ሥራ አስኪያጅ GERD የQR ኮድ ስካን የጎን አሞሌ የግንባታ ሳይቱን ለእንቅስቃሴ ማዘጋጀት እነዚህ ተሽከርካሪዎችን የሚያንቀሳቅሱ ሞተሮች፣ ለመሠረት ካምፖች የውሃ መሳቢያ እና የማከሚያ ሲስተም ነዳጅ የሚሰጡ ናቸው። የሚመሩት Franco Cetrangolo በተባሉት ጣሊያናዊ ዜጋ ሲሆን ግለሰቡ በWebuild Group ውስጥ ለዓመታት የሰሩ እና የGERD የማምረቻ ሥራ አስኪያጅ ናቸው። “ከፍተኛ ምርት ላይ በነበርንበት ወቅት” ሲሉ የሚገልጹት Cetrangolo “እጅግ አስፈላጊ ማሽኖችን ብቻ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከ5,500 ንብረቶች አልፈን ነበር።” ማምረቻው በተለያዩ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነዚህም፡ የአርማታ ማምረቻ፣ የማሰራጫ ሲስተሞች፣ ሞተሮች፣ ጎማዎች፣ የኤሌክትሪክ ሲስተሞች፣ እና የተሸከርካሪ አካል መስሪያዎች ናቸው። “እኛ’እዚህ ከሁሉ ነገር የራቅን ነን” ሲሉ የሚቀጥሉት” Cetrangolo “እናም አንዳንድ ጊዜ መለያየት በተግባር የማይቻል ነው። ስለዚህ ለግንባታው የሚያስፈልጉንን ሁሉ ነገሮች ያደራጀነው እኛው እራሳችን ነን።” ከፍተኛ ጊዜያት ላይ ስንደርስ ፒክ አፖችን፣ ሚኒባሶችን፣ አምቡላንሶችን ጨምሮ የ450 ተሽከርካሪዎችን እና ቡልዶዘሮችን፣ ኤክስካቫተሮችን እና የተለያዩ መሳሪያዎችን፣ ከ60 ቶኖች በላይ የመስሪያ ክብደት ያላቸው ትላልቅ ማሽኖችን ጨምሮ የ120 ማሽኖችን ስራ ላይ መዋል ለማረጋገጥ ከ 1,200 በላይ ሰዎች በሀይል ማመንጫው ውስጥ ሰርተዋል። በተጨናነቀው የGERD ከተማ ቤተ ሙከራ እና ማምርቻ ውስጥ ማንኛውም አይነት ማሽች ወደ ህይወት የሚመጡባቸው ቦታዎች ናቸው። 58

60 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 61 በለውጥ ላይ ለሚገኝ አህጉር የልብ ምት GERD ከግድብ በላይ ነው። ግድቡ የሽግግር ምዕራፍ ምልክት ነው። ሀገርን ወደ እንቅስቃሴ የከተተ፣ የስራ እድሎችን፣ ኢነርጂና ልማትን የፈጠረ ፕሮጀክት ነው። “በግንባታ ሳይቱ ላይ እያንዳንዱ ቀን ታሪክ ነው። ፈተና፣ ግኝት፣ ድል ነው” ሲሉ ኢንጂነር Capitanio አጠቃለዋል። “GERDን ገንብተናል፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ በአንድ ህዝብና ሀገር ውስጥ በራስ መተማመንን፣ የወደፊት ተስፋን እና ማንነትን ለመትከል አግዘናል።” ውጤቱም የሀገር ኩራት ምንጭ የሆነው መዋቅር ነው። • Lorem ipsum color dida ሁለቱ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫዎች በአጠቃላይ 5,150 ሜጋ ዋት የተተከለ አቅም ያላቸው እና በዓመት 15,700 ጊጋ ዋት በሰዓት ምርት እንደሚያመርቱ የሚጠበቁ 13 ፍራንሲስ ተርባይኖችን ያቀፉ ሲሆን ይህም ከሶስት መካከለኛ መጠን ያላቸው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ጋር እኩል ነው:: የማሽን አዳራሽ

63 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • የኮንክሪት/አርማታ ናሙናዎች የጎን አሞሌ ላብራቶሪ “የመጀመሪያው እና ከሁሉም የሚቀድመው የላብራቶሪው ተልዕኮ ለግድቦቹ ግንባታ እና በሁሉም የፕሮጀክቱ ሳይቶች ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉትን የግንባታ ዕቃዎች ማጥናት፣ መመርመር እና መተግበር ነው።” አማኑ እስመቱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ የGERD የላብራቶሪ ስራ አስኪያጅ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙት የWebuild Group የግንባታ ሳይቶች ላይ ለ30 ዓመታት ከመስራቱም በተጨማሪ 230 ሰዎችን የሚይዝ ቡድን ይመራል። የ GERD ላብራቶሪ ሁሉም ዕቃዎች በሳይት ላይ ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት የመሞከር ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ምክንያት ሥራቸው እጅግ ውስብስብ ነው። “አርማታ/ኮንክሪትን በተመለከተ” ሲሉ የሚያብራሩት አማኑ እስመቱ፣ “ምርመራዎችን ለማካሄድ ከ7 ቀናት አንስቶ እስከ 365 ቀናት የሚደርሱ የተለያዩ ቀነ ገደቦች አሉን። አርማታ የተለያዩ ቅርጾች - ጣሳ ቅርጽ፣ ፕሪዝም ወይም ኪዩብ - ባላቸው ናሙናዎች ተዘጋጅቶ በትላልቅ በውሀ በተሞሉ ታንከሮች ውስጥ የሚቀመጥ ሲሆን ከውጫዊ የአየር ጠባይ ለውጦች ጋር ተያይዞ በሁኔታው ላይ በየዕለቱ ክትትል ይደረግበታል።” በኋላ ላይ ለዋናው ግድብ RCC ጥቅም ላይ በሚውለው ሲሚንቶ ላይ ሙከራ ማድረግ የላብራቶሪው ስራ አንድ ክፍል ሲሆን በእያንዳንዱ ዕቃ ላይ ከውሀ አንስቶ እስከ ብረት በየዕለቱ ትንተና ይካሄዳል። የላብራቶሪው ተልዕኮ ሁሉንም በኋላ ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ ዕቃዎችን ማጥናት፣ መሞከር እና መተግበር ነው። አማኑ እስመቱ የላቦራቶሪ ሥራ አስኪያጅ GERD የQR ኮድ ስካን 62

64 65 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • የዋናው ግድብ እና የውሀ ማጠራቀሚያው የጀርባ እይታ

66 67 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • የዋናው ግድብ የላይኛው ተፋሰስ እይታ ከዝርዝር መዝጊያ በሮች ጋር

68 69 ምዕራፍ 2 | GERD፣ ከማይቻለው በላይ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም • /ሳድል ግድቡ፣ የአርማታ/ኮንክሪት ገጽታ ዝርዝር

5,150 ሜጋ ዋት -–-–-–- የማመንጨት አቅም 15,700 ጊጋ ዋት በሰዓት -–-–-–- ዓመታዊ የኃይል ምርት 1,800 ሜትር -–-–-–- የዋናው ግድብ የጎንዮሽ ርዝመት ~10.7 ሚሊዮን ሜትር ኩብ -–-–-–- የዋናው ግድብ ይዘት 170 ሜትር -–-–-–- የዋናው ግድብ ቁመት 1.3 ሚሊዮን -–-–-–- የኃይል ማመንጫው ስራ ሲጀምር የሚያስቀረው የ CO2 ልቀት/በዓመት GERD በቁጥር ሶማሊያ ጅቡቲ ኤርትrራ ሱዳን ጥቁር አባይ ደቡብ ሱዳን ኬንያ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ GERD

72 ምዕራፍ 3 WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም

74 ምዕራፍ 3 | በሰዎች ትከሻ ላይ ያረፈ WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም የGERD ታሪክ ከቴክኖሎጂ ልህቀት እና ከኢኮኖሚ እና ኢነርጂ ልማት ትሩፋት ባሻገር በፕሮጀክቱ የተሳተፉ ሴቶችና ወንዶች ታሪክ ነው። የግድቡን ሀሳብ የጸነሱት፣ የነደፉት፣ የገነቡት እና ሰፊውን የግንባታ ቦታ ወደ የተጨናነቀች ትንሽ ከተማ ለመቀየር ሁሉንም አገልግሎቶች ያቀረቡት ሰዎች ሁሉ ታሪክ። GERD በተጨማሪም ማህበራዊ ድርጅት ነው መዋቅሩን ለመገንባት Webuild ከምንም በመነሳት ትክክለኛ ከተማ ፈጥሯል: መንደሮች፣ የመኖሪያ ካምፖች፣ አገልግሎት መስጫዎች፣ የሎጅስቲክስ መሰረተ ልማት፣ የጤና እንክብካቤ ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች። “ወደዚህ ስንመጣ ምንም ነገር አልነበረም ” ሲሉ ይገልጻሉ ኢንጅነር Capitanio። “በአሁኑ ወቅት አገልግሎት መስጫዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴዎች፣ የዕደ ጥበብ ውጤቶች፣ ሬስቶራንቶች ያሉት እውነተኛ ማህበረሰብ ያለ ከመሆኑም በተጨማሪ ከ25,000 በላይ ሰራተኞች በፕሮጀክቱ ውስጥ የተሳተፉ ሲሆን በከፍተኛ ጊዜያት ላይ በአንድ ጊዜ እስከ 10,000 ሰዎች ተሳትፈዋል።” የሎጅስቲክስ መሰረተ ልማቱ እጅግ ማራኪ ነው: ሶስት የምግብ ጓዳዎች፣ ክበብ፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የእግር ኳስና ቴኒስ መጫወቻ ሜዳዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ሁለት የህክምና መሳሪያዎች የተሟሉላቸው ክሊኒኮች፣ ትምህርት ቤት፣ አዲስ የተገነባ አውሮፕላን ማረፊያ፣ እንጀራ ማምረቻ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤት እና ለሰራተኞች የሳተላይት የኢንተርኔት ግንኙነቶች አሉ። ይህ ሁሉ የተጀመረው በ2011 የነበረ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ እንቅስቃሴዎች የተጀመሩት በዚያን ጊዜ ሰው በሌለው እና ምቹ ባልሆነ አካባቢ ነበር። የመጀመሪያው ደረጃ ከቀሪው የሀገሪቱ ክፍል ጋር ግንኙነት መፍጠር ነበር። ለዚህም ቡድኖቹ ወደ ቦታው ለመድረስ የሚያስችል የመንገድ አውታር የመገንባት፣ ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጋር ፈጣን ግንኙነት ለመፍጠር የሚያስችል የአውሮፕላን ማረፊያ እና የወንዙን ዳርቻ ለማገናኘት ሁለት ድልድዮችን የመገንባት ኃላፊነት የተሰጣቸው ሲሆን ይህም ለወደፊቱ ግድብ ከአንደኛው ጎን ወደ ሌላኛው ጎን በቀላሉ መንቀሳቀስ ያስችላል። ከመንገድ አውታር ግንባታ ጎን ለጎን በከፍተኛ የሥራ ጊዜያት በአንድ ጊዜ እስከ 10,000 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ካምፖች ቅርጽ መያዝ ጀመሩ። ሶስት የተለያዩ ካምፖች የተፈጠሩ ሲሆን እነዚህም፡ የአካባቢው ካምፕ እና የሲኒየር ካምፕ የታችኛው ተፋሰስ በቅደም ተከተል ለሰራተኞች እና የበለጠ ልምድ ያላቸው የቡድን መሪዎች የሚያገለግሉ፣ እና ወደ ግድቡና ሀይቁ በሚያሳየው ኮረብታ ላይ የተገነባው በመጀመሪያ የውጭ ሀገር ዜጎችን እና በኋላ ላይም የኃይል ማመንጫውን ኦፕሬተሮች ለማስተናገድ የተገነባው ቋሚ ካምፕ ናቸው። በካምፖቹ ውስጥ ከሚኖሩት እና በግድቡ ግንባታ ላይ ከተሳተፉት ከ25,000 በላይ ሰዎች ውስጥ GERD ማህበራዊ ድርጅት ነው። በGERD የግንባታ ሳይት ላይ ከ25,000 በላይ ሰዎች የሚሰሩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ95% በላዩ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

76 WEBUILD | የሀገሪቱ ህልም 77 ምዕራፍ 3 | በሰዎች ትከሻ ላይ ያረፈ 95% ያክሉ ኢትዮጵያውያን በተለይም የአካባቢው ማህበረሰቦች ናቸው። ከመንገድ ግንባታው ጎን ለጎን ለጥቁር አባይ የውሀ አስተዳደርና ማከሚያ ተቋም ተገንብቷል። የወንዙ ውሀ በሁለት ትላልቅ ታንከሮች ይጠራቀም እና በአንድ በኩል ለሳይቱ ማሽኖች እና በሌላ በኩል ለነዋሪዎች በፓምፕ ከመሰራጨቱ በፊት ተከታታይ ህክምናዎች ይደረጉለታል። ውሀ እጅግ ወሳኝ ሀብት ሲሆን ትምህርትም እንደዚሁ ነው። ስለሆነም ግንባታው በተካሄደባቸው ዓመታት ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በካምፕ ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ ህጻናት ትምህርት ቤት የተቋቋመ ከመሆኑም በተጨማሪ ታዳጊዎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ይሰጡ ነበር። ለሁሉም ሰው አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታል፣ ክሊኒኮችና የጤና እንክብካቤ ተፈጥሮ ተንከባካቢ በሚፈልግበት እና ተግዳሮት በሆነበት እንደዚህ ባለ ገለልተኛ አካባቢ በሳይቱ ላይ ለሚሰሩ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የጤና አጠባበቅ አገልግሎትን ማረጋገጥ ከጅምሩ አስፈላጊ ነበር። መሳሪያዎች ከተሟሉላቸው የጤና እንክብካቤ ማዕከላት ያለውን ርቀት ከግምት ውስጥ በማስገባት Webuild ለሰራተኞች እርዳታ ከማድረግ በተጨማሪ በአቅራቢያው ላሉ ቦታዎች ነዋሪዎች ክፍት የሆነ የጤና እንክብካቤ መስጫ ስርዓት አቋቁሟል። ማዕከላዊ ሆስፒታል እና ሁለት ሳተላይት ክሊኒኮች ተገንብተዋል። 20 መኝታዎች፣ ስድስት አምቡላንሶች • የባምዛ መንደር የግንባታ ሳይቱ የመዝናኛ ቦታዎች፣ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል እና የምግብ ፋብሪካ ወዳለው አነስተኛ ከተማነት ተለውጧል።

RkJQdWJsaXNoZXIy MTI4OTY=